⚖️
Court Management System
Justice • Integrity • Excellence
Home
About Us
View Posts
Contact Us
Login
🌐 English
🇪🇹 Amharic
Oromiffa
Somali
Back to Posts
📰
sultan kedir •
May 10, 2026
የባልና ምስት ንብረት ክፍፍል
አንድ ንብረት ከጋብቻ በፊት የተፈራ የግል ሀብት ከሆነ፣ በባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ላይ የሁለቱም ተጋቢዎች ስም መመዝገቡ ብቻ ንብረቱን የጋራ እንደማያደርገው ወስኗል። ችሎቱ በውሳኔው እንደገለጸው፣ የማይንቀሳቀስ ንብረት የምስክር ወረቀት (ካርታ) የአንድን ሰው መብት ለማረጋገጥ የሚሰጥ ማስረጃ እንጂ በራሱ መብትን የማይፈጥር በመሆኑ፣ የግል ንብረትን ወደ ጋራ ለማዛወር የሚያስችል ሕጋዊ የጋብቻ ውል በሌለበት ሁኔታ በካርታ ላይ ስም ሰፍሮ መገኘቱ ብቻ ንብረቱን የጋራ ሊያደርገው አይችልም። በመሆኑም የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 42፣ 57 እና 85ን እንዲሁም የፍትሐብሔር ሕግ አንቀጽ 1195 እና 1196ን መሠረት በማድረግ፣ ከጋብቻ በፊት በግል ጥረት የተፈራ ንብረት በስም ዝውውር ወይም በካርታ ላይ ስም በመጨመር ብቻ ወደ ጋራ ሀብትነት እንደማይለወጥ ችሎቱ አረጋግጧል።\r\n✅የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 245844 የሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል።