Back to Posts
📰

ዜና

#የጦራ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከወረቀት ነፃ የሆነ አገልግሎት በአንድ ማዕከል እንዲሰጥ የማያስችል የዌብሳይት አገልግሎት ማስጀመሩን ገለፀ!!\r\n\r\nበዌብሳይት አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃግብሩ ላይ የጦራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ካሚል አማን ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።\r\n\r\nከንቲባው የዌብሳይት አገልግሎቱ በይፋ መጀመሩን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት ፍ/ቤቱ አገልግሎቱን ለማዘመንና ለተገልጋዮች ፈጣንና ሚዛናዊ አገልግሎት ለመስጠት የሚያደርጋቸው ጥረቶች የሚደነቁ መሆኑን ተናግረዋል።\r\n\r\nከንቲባው አክለውም የፍርድ ቤቱን አገልግሎት ለማዘመንና የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል አስፈላጉጊ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።\r\n\r\nየጦራ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ሱልጣን ከድር በፕሮግራሙ ላይ እንደገለፁት ዌብሳይቱ ሙሉበሙሉ በሚባል ደረጃ የፍ/ቤቱን አገልግሎት ከወረቀት ነፃ ማድረግ የሚያስችል እንደሆነ በመግለፅ ይህም ለፍ/ቤቱና ለተገልጋዮች አላስፈላጊ ወጪን የሚያስቀረ እንደሆነ ገልጸዋል።\r\n\r\nበዌብሳይቱ በኦንላይን አዲስ ኬዝ መመዝገብ፣ለተመዘገበው ኬዝ ቀጠሮ መስጠት፣ሪፖርት መፃፍ ፣ ውሰኔ የገኙ መዝገቦዎችን እስካን በመድረግና በስስተሙ በመጫን ባለጉዳዮች ባሉበት ቦታ ሆነው በኦንላይን ጥያቄ በመቅረብ በቀጥታ በአድራሸቸው የሚለክለቸው እንደሆነና ሌሎችም ተያያዥ አገልግሎቶችን ለተገልጋዮች ባሉበት ሆነው መስጠት የሚያስችል በመሆኑ ተገልጋዮች ከአላስፈላጊ እንግልት የሚያድን እንደሆነና በተጨማሪም በቀጣይ የኦንላይን ችሎት ለማስጀመር ተቋሙ ከሚመለከታቸው አካለት ጋር እየሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል ።\r\n\r\nፕሬዝዳንቱ በማጠቃሊያቸው ዌብሳይቱን በማበልፀግ አገልግሎት እንዲሰጥ ያደረገው የጦራ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።\r\n\r\nበፕሮግራሙ ላይ የጦራ ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ደኑር ኮሪ፣የጦራ ከተማ አስተዳደር ዋና አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ እልፍነሽ አወልን ጨምሮ ሌሎችም ጥሪ የተደረገላየው እንግዶችና የፍ/ቤቱ ዳኞችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።\r\nበመጨረሻም በዌብሳይት ማበልፀግ ሂደቱ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የነበራየው ተቋማት እውቅና በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል።\r\n\r\nዌብሰይቱን ለመግኛት \r\nhttps://tcjuoffice.gov.et/